Thursday, May 29, 2014

ኢትዮ ቴሌኮም የኔትወርክ መቆራረጡን ከመብራት መቆራረጥ ጋር የተያያዘ ነው አለ፡፡

| ኢትዮ ቴሌኮም የኔትወርክ መቆራረጡን ከመብራት መቆራረጥ ጋር የተያያዘ ነው አለ፡፡
ሰሞኑን በአዲስ አበባና በክልሎች በርካታ የኔትወርክ መቆራርጥና መጥፋት የተከሰተው በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ በማጋጠሙ መሆኑን የኩባንያው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድን ጠቅሶ ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
እንደ አቶ አብዱራሂም ገለጻ ችግሩን ለመፍታት ኢትዮቴሌኮም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፕሬሸን ጋር እየተነጋገረ ሲሆን ከዚህ ውጪም ይህ ችግር እንዳይከሰት ለማድለግ የኤሌክትሪክ ሀይል ቢቋረጥ እንኳን የቴሌኮም አገልግሎት እንዳይቋረጥ የሚያደርግ ድጋፍ ሰጪ መሳሪያዎች በአዲሱ ማስፋፊያ እየተዘረጋ ነው፡፡
ከዚህ ውጪ ግን አሁን ኢትዮቴሌኮም እያካሄደ ካለው ማስፋፊያ ጋር በተያያዘ የኔትዎርክ መቆራረጥ ችግር ያልተፈጠረ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ የኔትዎርክ ማስፋፊያ በሶስት ምእራፎች የተከፋፈለ መሆኑን የገለጹት ሃላፊው፤ የመጀመሪያው የኖኪያ የኔትዎርክ የሚባሉ አካባቢዎችን በአዲስ መቀየር ሲሆን ሁሉም የኖክያ አካባቢዎች በአዲሱ ቴክኖሎጂ የተቀየሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በሁለተኛው ደረጃ የአዲስ አበባ ኔትዎርክ ሙሉ በሙሉ መቀየር ሲሆን ይህም ስራ ሙሉ በሙሉ የተከናወነ መሆኑን ተመልክቷል፡፡
ለዝርዝሩ

No comments:

Post a Comment